bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 146
Psalms 146
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።
2
በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
3
በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ ሥጋ ለባሾችም አትመኩ።
4
መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤ ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል።
5
ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው ምስጉን ነው፤
6
እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በእነዚህም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ፣ ታማኝነቱንም ለዘላለም የሚጠብቅ ነው፤
7
ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤
8
እግዚአብሔር የዕውራንን ዐይን ያበራል፤ እግዚአብሔር የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤
9
እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤ ድኻ ዐደጎችንና መበለቶችን ይደግፋል፤ የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል።
10
እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል፤ ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው። ሃሌ ሉያ።
← Chapter 145
Chapter 147 →