bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 120
Psalms 120
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ።
2
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ ከአታላይ ምላስም አድነኝ።
3
ሐሰተኛ አንደበት ሆይ፤ ምን ይከፈልህ? ከዚህስ የባሰ ምን ይደረግብህ?
4
በተሳለ የጦረኛ ቀስት፣ በግራር ከሰል ፍም ይቀጣሃል።
5
በሜሼክ እኖራለሁና፣ በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ!
6
ሰላምን በሚጠሉ መካከል፣ ነፍሴ እጅግ ብዙ ጊዜ ኖረች።
7
እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፤ እነርሱ ግን በተናገርሁ ጊዜ ጠብ ይሻሉ።
← Chapter 119
Chapter 121 →