bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Proverbs 7
Proverbs 7
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ጠብቅ፤ ትእዛዜንም በውስጥህ አኑር።
2
ትእዛዜን ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ ትምህርቴንም እንደ ዐይንህ ብሌን ተንከባከበው።
3
በጣትህ ላይ እሰረው፤ በልብህ ጽላት ላይ ጻፈው።
4
ጥበብን፣ “እኅቴ ነሽ” በላት፤ ማስተዋልንም፣ “ዘመዴ ነህ” በለው፤
5
ከአመንዝራ ሴት፣ በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ሴት ይጠብቁሃል።
6
በቤቴ መስኮት፣ በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ።
7
ማስተዋል የጐደለውን ወጣት፣ ብስለት ከሌላቸው መካከል አየሁት፤ ከጕልማሶችም መካከል ለየሁት።
8
የቤቷን አቅጣጫ ይዞ፣ በቤቷ ማእዘን አጠገብ ባለው መንገድ ያልፍ ነበር፤
9
ቀኑ መሸትሸት ሲል፣ በውድቅት ሌሊት፣ በጽኑ ጨለማ።
10
ከዚያም አንዲት ሴት ልታገኘው ወጣች፤ እንደ ዝሙት ዐዳሪ ለብሳ፣ ለማሳሳት ታጥቃ።
11
ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤ እግሮቿ ዐርፈው ቤት አይቀመጡም፤
12
አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ፣ በየማእዘኑም ታደባለች።
13
አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ ኀፍረቷንም ጥላ እንዲህ አለችው፤
14
“በቤቴ የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ፤
15
ስለዚህ አንተን ለማግኘት ወጣሁ፤ ፈልጌህ ነበር፤ ይኸው አገኘሁህ።
16
ዐልጋዬን ከግብፅ የመጣ፣ ጌጠኛ በፍታ አልብሼዋለሁ።
17
ዐልጋዬን፣ የከርቤ፣ የዓልሙንና የቀረፋ ሽቱ አርከፍክፌበታለሁ።
18
ና፤ እስኪነጋ በጥልቅ ፍቅር እንርካ፤ በፍቅር ራሳችንን እናስደስት።
19
ባሌ እቤት የለም፤ ሩቅ አገር ሄዷል።
20
በገንዘብ የተሞላ ቦርሳ ወስዷል፤ ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን አይመለስም።”
21
በሚያግባቡ ቃላት አሳተችው፤ በለሰለሰ አንደበቷ አታለለችው።
22
ለዕርድ እንደሚነዳ በሬ፣ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ አጋዘን፣ ሳያንገራግር ተከተላት፤
23
ፍላጻ ጕበቱን እስኪወጋው ድረስ፣ ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ፣ በርራ ወደ ወጥመድ እንደምትገባ ወፍ ሆነ።
24
ልጆቼ ሆይ፤ አሁንም አድምጡኝ፤ የምለውንም ልብ ብላችሁ ስሙኝ።
25
ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ፤ ወደ ስሕተት ጐዳናዋም አትግቡ።
26
አዋርዳ የጣለቻቸው ብዙ ናቸው፤ የገደለቻቸውም ስፍር ቍጥር የላቸውም።
27
ቤቷ ወደ ሲኦል የሚወስድ፣ ወደ ሞት ማደሪያም የሚያወርድ ጐዳና ነው።
← Chapter 6
Chapter 8 →