bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Proverbs 31
Proverbs 31
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ንጉሥ ልሙኤልን እናቱ ያስተማረችው ቃል ይህ ነው፤
2
“ልጄ ሆይ፤ የማሕፀኔ ልጅ ሆይ፤ የስእለቴ ልጅ ሆይ፤
3
ጕልበትህን በሴት አትጨርስ፤ ብርታትህንም ነገሥታትን ለሚያጠፉ አታውል።
4
“ልሙኤል ሆይ፤ ነገሥታት ይህን ማድረግ የለባቸውም፤ ነገሥታት የወይን ጠጅ ሊጠጡ፣ ገዦችም የሚያሰክር መጠጥ ሊያስጐመጃቸው አይገባም፤
5
አለዚያ ጠጥተው የሕጉን ድንጋጌ ይረሳሉ፤ የተጨቈኑትን ሁሉ መብት ይገፍፋሉ።
6
ለሚጠፉት የሚያሰክር መጠጥ፣ በሥቃይ ላሉትም የወይን ጠጅ ስጧቸው፤
7
ጠጥተው ድኽነታቸውን ይርሱ፤ ችግራቸውንም ከእንግዲህ አያስቡ።
8
“ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣ ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት።
9
ተናገር፤ በቅንነትም ፍረድ፤ የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”
10
ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንእጅግ ትበልጣለች።
11
ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤ የሚጐድልበትም ነገር የለም።
12
በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣ መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም።
13
የበግ ጠጕርና የተልባ እግር መርጣ፣ ሥራ በሚወዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች።
14
እንደ ንግድ መርከብ፣ ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች።
15
ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች።
16
ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤ በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች።
17
ብርታትን ታጥቃ ሥራዋን ታከናውናለች፤ ክንዶቿም ለሥራ ብርቱ ናቸው።
18
ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤ በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም።
19
በእጇ እንዝርት ትይዛለች፤ በጣቶቿም ዘንጉን ታሾራለች።
20
ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣ እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች።
21
በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤ ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና።
22
ለመኝታዋ የዐልጋ ልብስ ትሠራለች፤ ቀጭን በፍታና ሐምራዊ ልብስ ለብሳለች።
23
ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከል በአደባባይ በተቀመጠ ጊዜ የተከበረ ነው።
24
የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች።
25
ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤ መጭውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች።
26
በጥበብ ትናገራለች፤ በአንደበቷም ቀና ምክር አለ።
27
የቤተ ሰቦቿን ጕዳይ በትጋት ትከታተላለች፤ የስንፍና እንጀራ አትበላም።
28
ልጆቿ ተነሥተው ቡርክት ይሏታል፤ ባሏም እንዲሁ፣ ሲያመሰግናትም እንዲህ ይላል፤
29
“ብዙ ሴቶች መልካም አድርገዋል፤ አንቺ ግን ሁሉንም ትበልጫለሽ።”
30
ቍንጅና አታላይ ነው፤ ውበትም ይረግፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን የተመሰገነች ናት።
31
የሚገባትን ሽልማት ስጧት፤ ሥራዋም በየአደባባዩ ያስመስግናት።
← Chapter 30