bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Proverbs 17
Proverbs 17
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ጠብ እያለ ግብዣ ከሞላበት ቤት ይልቅ፣ በሰላምና በጸጥታ የእንጀራ ድርቆሽ ይሻላል።
2
ጠቢብ አገልጋይ በወራዳ ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ ከወንድማማቾቹም እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።
3
ማቅለጫ ለብር፣ ከውር ለወርቅ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመረምራል።
4
እኩይ ሰው ክፉ ንግግር ያዳምጣል፤ ሐሰተኛም የተንኰለኛን አንደበት በጥንቃቄ ይሰማል።
5
በድኾች የሚያፌዝ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ በሌላው ሰው መከራ ደስ የሚለው ከቅጣት አያመልጥም።
6
የልጅ ልጆች ለአረጋውያን ዘውድ ናቸው፤ ወላጆችም ለልጆቻቸው አለኝታ ናቸው።
7
መልካም አነጋገር ለተላላ አይሰምርለትም፤ ለገዥማ ሐሰተኛ አንደበት የቱን ያህል የከፋ ይሆን!
8
እጅ መንሻ ለሰጭው እንደ ድግምት ዕቃ ነው፤ በሄደበትም ቦታ ሁሉ ይሳካለታል።
9
በደልን የሚሸፍን ፍቅርን ያዳብራል፤ ነገርን የሚደጋግም ግን የልብ ወዳጆችን ይለያያል።
10
መቶ ግርፋት ተላላን ከሚሰማው ይልቅ፣ ተግሣጽ ለአስተዋይ ጠልቆ ይሰማል።
11
ክፉ ሰው ዐመፅን ብቻ ይፈልጋል፤ በእርሱም ላይ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።
12
ተላላን በቂልነቱ ከመገናኘት፣ ግልገሎቿን የተነጠቀችን ድብ መጋፈጥ ይሻላል።
13
በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልስ ሰው፣ ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።
14
ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።
15
በደለኛውን ንጹሕ ማድረግ ሆነ፣ ንጹሑን በደለኛ ማድረግ፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ናቸው።
16
ጥበብን ለማግኘት ፍላጎት ስለሌለው፣ ተላላ እጅ የገባ ገንዘብ ጥቅሙ ምንድን ነው?
17
ወዳጅ ምንጊዜም ወዳጅ ነው፤ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል።
18
ማስተዋል የጐደለው ሰው ቃል በመግባት እጅ ይመታል፤ ለወዳጁም ዋስ ይሆናል።
19
ጠብ የሚወድድ ኀጢአትን ይወድዳል፤ በሩን ከፍ አድርጎ የሚሠራም ጥፋትን ይጋብዛል።
20
ጠማማ ልብ ያለው ሰው አይሳካለትም፤ በአንደበቱ የሚቀላምድም መከራ ላይ ይወድቃል።
21
ተላላ ልጅ መውለድ ሐዘን ያስከትላል፤ የተላላም አባት ደስታ የለውም።
22
ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኀኒት ነው፤ የተሰበረ መንፈስ ግን ዐጥንትን ያደርቃል።
23
ክፉ ሰው ፍትሕ ለማዛባት፣ በስውር ጕቦ ይቀበላል።
24
አስተዋይ ሰው ጥበብን ከፊቱ አይለያትም፤ የተላሎች ዐይኖች ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታሉ።
25
ተላላ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤ ለወለደችውም ምሬት ይሆንባታል።
26
ንጹሑን ሰው መቅጣት ተገቢ አይደለም፤ ሹሞችን ስለ ቅንነታቸው መግረፍ መልካም አይደለም።
27
ዐዋቂ ሰው ንግግሩ ቍጥብ ነው፤ አስተዋይም መንፈሱ የረጋ ነው።
28
አላዋቂ እንኳ ዝም ቢል ጠቢብ፣ አንደበቱንም ቢገዛ አስተዋይ ይመስላል።
← Chapter 16
Chapter 18 →