bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Micah 6
Micah 6
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ፤ “ተነሡ፤ ጕዳያችሁን በተራሮች ፊት አቅርቡ፤ ኰረብቶች እናንተ የምትሉትን ይስሙ፤
2
“ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ክስ አድምጡ፤ እናንት የምድር ጽኑ መሠረቶችም፣ ስሙ፤ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፤ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳል።
3
“ሕዝቤ ሆይ፤ ምን አድርጌሃለሁ? ሸክም የሆንሁብህስ እንዴት ነው? እስቲ መልስልኝ!
4
ከግብፅ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤ እንዲመሩህ ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።
5
ሕዝቤ ሆይ፤ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፣ የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትንም እስቲ አስቡ፤ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራ ታውቁ ዘንድ፣ ከሰጢም እስከ ጌልገላ የተጓዛችሁትን ዐስቡ።”
6
ምን ይዤ በእግዚአብሔር ፊት ልቅረብ፣ በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ ከአንድ ዓመት ጥጃ ጋር ይዤ በፊቱ ልቅረብን?
7
በአንድ ሺሕ አውራ በጎች፣ በዐሥር ሺሕ የዘይት ፈሳሽ እግዚአብሔር ደስ ይለዋልን? ስለ በደሌ የበኵር ልጄን፣ ስለ ነፍሴም ኀጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብለትን?
8
ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣ በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?
9
ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፤ ስሙ! እግዚአብሔር ከተማዪቱን እንዲህ እያለ ይጣራል፤ “በትሩን አስቡ፤ ያዘጋጀውም ማን እንደ ሆነ አስታውሱ ።
10
የክፋት ቤት ሆይ፤ በግፍ የተገኘ ሀብታችሁን፣ በሐሰተኛ መስፈሪያ የሰበሰባችሁትን አስጸያፊ ነገር እረሳዋለሁን?
11
አባይ ሚዛን የያዘውን ሰው፣ ሐሰተኛ መመዘኛ በከረጢት የቋጠረውን ንጹሕ ላድርገውን?
12
ባለጠጎቿ ግፈኞች፣ ሰዎቿ ሐሰተኞች ናቸው፤ ምላሳቸውም አታላይ ናት።
13
ስለዚህ አንተን አጠፋሃለሁ፣ ከኀጢአትህ የተነሣ አፈራርስሃለሁ።
14
ትበላለህ፤ ነገር ግን አትጠግብም፤ ሆድህ እንዳለ ባዶውን ይቀራል፤ ታከማቻለህ፤ ነገር ግን አይጠራቀምልህም፤ የሰበሰብኸውን ለሰይፍ አደርገዋለሁና።
15
ትዘራለህ፤ ነገር ግን አታጭድም፤ የወይራ ዘይት ትጨምቃለህ፤ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይንን ትቈርጣለህ፤ ነገር ግን የወይን ጠጅ አትጠጣም።
16
የዖምሪን ሥርዐት፣ የአክዓብን ቤት ልምድ ሁሉ የሙጥኝ ብለሃል፤ ትውፊታቸውንም ተከትለሃል። ስለዚህ አንተን ለውድመት፣ ሕዝብህን ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ አሕዛብም ይሣለቁብሃል ።”
← Chapter 5
Chapter 7 →