bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Leviticus 21
Leviticus 21
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤
2
ነገር ግን የቅርብ ዘመዶቹ ስለ ሆኑት እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣ ወይም ወንድሙ፣
3
እንዲሁም ባለማግባቷ ከእርሱ ጋር ስለምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል።
4
ከእርሱ ጋር በጋብቻ ለሚዛመዱት ግን ራሱን አያርክስ።
5
“ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤
6
ለአምላካቸው (ኤሎሂም) የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም (ኤሎሂም) ስም አያርክሱ። ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን (ኤሎሂም) ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ።
7
“ ‘ካህናት በዝሙት የረከሱትንም ሆነ ከባሎቻቸው የተፋቱትን ሴቶች አያግቡ፤ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም) የተቀደሱ ናቸውና።
8
የአምላክህን (ኤሎሂም) ምግብ የሚያቀርብ ነውና ቀድሰው፤ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ቅዱስ ነኝና ቅዱስ ይሁንላችሁ።
9
“ ‘የካህን ሴት ልጅ ዝሙት ዐዳሪ ሆና ራሷን ብታረክስ፣ አባቷን ታዋርዳለች፤ በእሳት ትቃጠል።
10
“ ‘ከወንድሞቹ መካከል ተለይቶ በራሱ ላይ ዘይት የፈሰሰበትና የክህነት ልብስ እንዲለብስ የተቀባው ካህን የራስ ጠጕሩን አይንጭ፤ ወይም ልብሱን አይቅደድ።
11
አስከሬን ወዳለበት ስፍራ አይግባ፤ ስለ አባቱም ሆነ ስለ እናቱ ራሱን አያርክስ፤
12
የተቀደሰበት የአምላኩ (ኤሎሂም) የቅባት ዘይት በላዩ ስለሆነ የአምላኩን (ኤሎሂም) መቅደስ ትቶ በመሄድ መቅደሱን አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።
13
“ ‘ካህኑ የሚያገባት ሴት ድንግል ትሁን።
14
ባል የሞተባትን፣ የተፋታችውን ወይም በዝሙት ዐዳሪነት የረከሰችውን ሴት አያግባ፤ ነገር ግን ከወገኖቹ መካከል ድንግሊቱን ያግባ።
15
በወገኖቹ መካከል ዘሩን አያርክስ። እርሱን የምቀድሰው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”
16
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
17
“አሮንን እንዲህ በለው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይሠዋ ዘንድ አይቅረብ።
18
ዕውር ወይም ዐንካሳ፣ የፊቱ ገጽታ ወይም የሰውነቱ ቅርጽ የተበላሸ ማንኛውም የአካል ጕድለት ያለበት ሰው አይቅረብ።
19
እንዲሁም እግሩ ወይም እጁ ሽባ የሆነ፣
20
ጐባጣ ወይም ድንክ፣ ማንኛውም ዐይነት የዐይን እንከን ያለበት፣ የሚያዥ ቍስል ወይም እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ አይቅረብ።
21
ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጕድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለሆነ፣ የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ለማቅረብ አይምጣ።
22
እርሱም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይብላ።
23
ነገር ግን እንከን ያለበት ስለሆነ መቅደሴን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይቅረብ ወይም ወደ መሠዊያው አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”
24
ሙሴም ይህን ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን ሁሉ ነገራቸው።
← Chapter 20
Chapter 22 →