bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Joshua 16
Joshua 16
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ለዮሴፍ ዝርያዎች የተመደበው ድርሻ፣ ከዮርዳኖስ ኢያሪኮ ፣ ማለት ከኢያሪኮ ምንጮች በስተ ምሥራቅ ይነሣና፣ ምድረ በዳውን በማቋረጥ በኰረብታማው አገር አድርጎ ወደ ቤቴል ይወጣል።
2
ሎዛ ከምትባለው ከቤቴል ይነሣና በአጣሮት ወደሚገኘው ወደ አርካውያን ግዛት ይሻገራል፣
3
በዚያም በምዕራብ በኩል ቍልቍል ወደ የፍሌጣውያን ግዛት እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ምድር ይወርድና ወደ ጌዝር ዘልቆ ባሕሩ ላይ ይቆማል።
4
ስለዚህ የዮሴፍ ዘሮች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ተቀበሉ።
5
ለኤፍሬም ወገን በየጐሣ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፤ ድንበሩ በምሥራቅ በኩል ከአጣሮት አዳር ተነሥቶ እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣና፣
6
እስከ ባሕሩ ይዘልቃል። በስተ ሰሜን ደግሞ ከሚክምታት ተነሥቶ በምሥራቅ በኩል ወደ ተአናት ሴሎ ይታጠፍና ከዚያ በማለፍ እስከ ኢያኖክ ምሥራቅ ይዘልቃል።
7
ከኢያኖክም በመነሣት ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ቍልቍል ይወርድና በኢያሪኮ በኩል አድርጎ ዮርዳኖስ ላይ ብቅ ይላል።
8
ድንበሩ አሁንም ከታጱዋ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ቃና ወንዝ ይወርድና ከባሕሩ ላይ ይቆማል። እንግዲህ የኤፍሬም ነገድ በየጐሣ በየጐሣቸው የተካፈሉት ርስት ይህ ነበር።
9
ይህም በምናሴ ነገድ ርስት ውስጥ ለኤፍሬም ዘሮች የተመደቡትን ከተሞች በሙሉና መንደሮቻቸውን የሚያጠቃልል ነው።
10
ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋር አብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።
← Chapter 15
Chapter 17 →