bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 36
Job 36
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፤
2
“በእግዚአብሔር ፈንታ ሆኜ የምለው አለኝ፤ ጥቂት ታገሠኝና እነግርሃለሁ።
3
ዕውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፤ ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደ ሆነ እገልጻለሁ።
4
ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋር ነው።
5
“እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ግን ማንንም አይንቅም፤ ኀያል፣ በዐላማውም ጽኑ ነው።
6
ክፉዎችን በሕይወት አያኖርም፤ ለተቸገሩት ግን በቅን ይፈርዳል።
7
ዐይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሣም፤ ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ ለዘላለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።
8
ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣ በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣
9
በእብሪት የፈጸሙትን በደል፣ ተግባራቸውን ይነግራቸዋል።
10
ተግሣጽን እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል፤ ከክፋታቸውም እንዲመለሱ ያዝዛቸዋል።
11
ታዝዘው ቢያገለግሉት፣ ቀሪ ዘመናቸውን በተድላ፣ ዕድሜያቸውንም በርካታ ይፈጽማሉ።
12
ባይሰሙ ግን፣ በሰይፍ ይጠፋሉ፤ ያለ ዕውቀትም ይሞታሉ።
13
“ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ፣ ቍጣን ያስተናግዳሉ፤ በሰንሰለት ባሰራቸውም ጊዜ እንኳ ወደ እርሱ አይጮኹም።
14
በቤተ ጣዖት ውስጥ ዝሙት በሚፈጽሙት መካከል፣ ገና በወጣትነታቸው ይቀጫሉ።
15
ነገር ግን የሚሠቃዩትን ከሥቃያቸው ያድናቸዋል፤ በመከራቸውም ውስጥ ይናገራቸዋል።
16
“አንተንም ከመከራ መንጋጋ፣ ጭንቀት ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ፣ ምርጥ ምግብ ወደ ሞላበት ማእድ ያወጣሃል።
17
አሁን ግን ለክፉዎች የሚገባው ፍርድ በላይህ ተጭኗል፤ ፍርድና ብይን ይዘውሃል።
18
ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣ የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።
19
ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?
20
ሰዎች ከቤታቸው የሚወሰዱበትን፣ ሌሊት አትመኝ።
21
ከመከራ ይልቅ መርጠኸዋልና፣ ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
22
“እነሆ፤ እግዚአብሔር በኀይሉ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?
23
እርሱን መንገድ የሚመራው፣ ወይም ‘ይህን አጥፍተሃል’ የሚለው ማን ነው?
24
ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣ የእርሱን ሥራ ማወደስ አትዘንጋ።
25
ሰው ሁሉ አይቶታል፤ ሰዎችም በትኵረት ተመልክተውታል።
26
እነሆ፤ እግዚአብሔር ከአእምሯችን በላይ ታላቅ ነው! የዘመኑም ቍጥር ከመታወቅ ያልፋል።
27
“የውሃን ነጠብጣብ ወደ ላይ ያተንናል፤ መልሶም በዝናብ መልክ በጅረቶች ላይ ያወርዳል፤
28
ደመናት ጠል ያንጠባጥባሉ፤ ዶፍም በሰው ላይ ይወርዳል።
29
ደመናትን እንዴት እንደሚዘረጋ፣ ከድንኳኑም እንዴት እንደሚያንጐደጕድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?
30
መብረቁን በዙሪያው እንዴት እንደሚበትን ተመልከት፤ የባሕሩንም ወለል ይሸፍናል።
31
እርሱ ሕዝብን የሚያስተዳድረው፣ ምግብንም አትረፍርፎ የሚሰጣቸው በዚህ መንገድ ነው።
32
እጆቹን በመብረቅ ይሞላቸዋል፤ ዒላማውንም እንዲመታ ያዝዘዋል።
33
ነጐድጓዱ ውሽንፍር እንደሚከተለው ያመለክታል፤ ከብቶችም እንኳ መምጣቱን ይጠቍማሉ።
← Chapter 35
Chapter 37 →