bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 35
Job 35
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ኤሊሁ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤
2
“ ‘በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕ ነኝ’ ማለትህ፣ ትክክል ይመስልሃልን?
3
ደግሞ ‘ያገኘሁት ጥቅም ምንድን ነው? ኀጢአት ባለ መሥራቴስ ምን አተረፍሁ?’ ብለህ ጠይቀኸዋል።
4
“ለአንተና አብረውህ ላሉት ባልንጀሮችህ፣ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ።
5
ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤ ከአንተ በላይ ከፍ ብለው ያሉትንም ደመናት ተመልከት።
6
ኀጢአትህስ ቢበዛ እርሱን ምን ትጐዳዋለህ? ኀጢአትህስ ቢበዛ ምን ያደርገዋል?
7
ጻድቅ ብትሆንም ለእርሱ ምን ትሰጠዋለህ? ከእጅህስ ምን ይቀበላል?
8
ክፋትህ የሚጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤ ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጆች ብቻ ነው።
9
“ሰው ከጭቈና ብዛት የተነሣ ይጮኻል፤ ከኀያሉም ክንድ ሥር ለመውጣት ለርዳታ ይጣራል።
10
ነገር ግን እንዲህ የሚል የለም፤ ‘ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? በሌሊት መዝሙርን የሚሰጥ፣
11
ከምድር እንስሳት ይልቅ የሚያስተምረን፣ ከሰማይ ወፎችም ይልቅ ጠቢባን የሚያደርገን፣ እርሱ የት አለ?’
12
ከዐመፀኞች ትዕቢት የተነሣ፣ ሰዎች ሲጮኹ አይመልስላቸውም፤
13
በርግጥ እግዚአብሔር ከንቱ ጩኸታቸውን አይሰማም፤ ሁሉን የሚችል አምላክ አያዳምጣቸውም።
14
ጕዳይህን ፊቱ አቅርበህ፣ ብዙ ጠብቀኸው፣ ግን እንዳላየኸው ስትናገር፣ ታዲያ፣ አንተን እንዴት ይስማህ!
15
ደግሞም፣ ቍጣው ቅጣት እንደማያስከትል፣ ኀጢአትንም ከቍጥር እንደማያስገባ ተናግረሃል።
16
ስለዚህ ኢዮብ አፉን በከንቱ ይከፍታል፤ ዕውቀት አልባ ቃላትም ያበዛል።”
← Chapter 34
Chapter 36 →