bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 23
Job 23
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
2
“ዛሬም ሐዘኔ መራራ ነው፤ እያቃሰትሁ እንኳ እጁ በላዬ ከብዳለች።
3
እርሱን የት እንደማገኘው ባወቅሁ፤ ወደ መኖሪያውም መሄድ በቻልሁ!
4
ጕዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤ አፌንም በሙግት እሞላው ነበር።
5
የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደ ሆነ ባወቅሁ ነበር፤ የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር።
6
በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋር ይሟገት ይሆን? አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል።
7
ቅን ሰው ጕዳዩን በእርሱ ፊት ያቀርባል፤ እኔም ከፈራጄ ለዘላለም ነጻ እሆናለሁ።
8
“ዳሩ ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ፣ በዚያ የለም፤ ወደ ምዕራብም ብሄድ፣ እርሱን አላገኘውም፤
9
በሰሜን እየሠራ ሳለ አላየውም፤ ወደ ደቡብ በሚዞርበት ጊዜ ደብዛው አይገኝም።
10
ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።
11
እግሮቼ ርምጃውን በጥብቅ ተከታትለዋል፤ ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ።
12
ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣ የአንደበቱን ቃል ከዕለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ።
13
“እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው? እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል።
14
በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው።
15
በፊቱ የደነገጥሁትም ለዚህ ነው፤ ይህን ሁሉ ሳስብ እፈራለሁ።
16
እግዚአብሔር ልቤን አባባው፤ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደነገጠኝ።
17
ይህም ሆኖ ሳለ ጨለማው፣ ፊቴንም የጋረደው ጽልመት ልሳኔን አልዘጋውም።
← Chapter 22
Chapter 24 →