bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 22
Job 22
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ቴማናዊውም ኤልፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ፤
2
“ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅም ይችላልን? ጠቢብ እንኳ ቢሆን ምን ይጠቅመዋል?
3
አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን የሚችለውን አምላክ ምን ደስ ታሰኘዋለህ? መንገድህ ያለ ነቀፋ ቢሆንስ የሚተርፈው ምንድን ነው?
4
“እርሱ የሚገሥጽህ፣ ፍርድ ቤትም የሚያቀርብህ ስለምትፈራው ነውን?
5
ክፋትህ ታላቅ፣ ኀጢአትህ ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?
6
ያለ አንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ መያዣ ወስደሃል፤ ሰዎችን ገፍፈህ፣ ያለ ልብስ ዕራቍታቸውን አስቀርተሃል።
7
የዛሉትን ውሃ አላጠጣህም፤ የተራቡትንም ምግብ ከልክለሃል።
8
ባለ ርስትና ኀያል፣ በእርሱም የምትኖር ክቡር ሰው ብትሆንም፣
9
መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰድደሃል፤ የድኻ ዐደጎችንም ክንድ ሰብረሃል።
10
ድንገተኛ አደጋ ያናወጠህ፣ ወጥመድም ዙሪያህን የከበበህ ለዚህ ነው።
11
እንዳታይ ጨለማ የሆነብህ፣ ጐርፍም ያጥለቀለቀህ ለዚህ ነው።
12
“እግዚአብሔር ከፍ ባለው ሰማይ የሚኖር አይደለምን? በሩቅ ከፍታ ያሉትን ከዋክብት ያያል!
13
ይህም ሆኖ ሳለ እንዲህ አልህ፤ ‘እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በእንዲህ ያለ ጨለማ ውስጥስ ይፈርዳልን?
14
በሰማይ ክበብ ላይ ሲራመድ፣ እንዳያየን ጥቅጥቅ ያለ ደመና ይሸፍነዋል።’
15
ኀጢአተኞች በሄዱባት፣ በጥንቷ መንገድ እንደ ተመላለስህ ትቀራለህን?
16
ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም በጐርፍ ተወሰደ።
17
እግዚአብሔርንም ‘አትድረስብን! ሁሉን የሚችል አምላክም ምን ያደርግልናል?’ አሉ።
18
ቤታቸውን በመልካም ነገር የሞላው ግን እርሱ ነው፤ ስለዚህ ከኀጢአተኞች ምድር እርቃለሁ።
19
“ጻድቃንም የእነዚያን ጥፋት አይተው ይደሰታሉ፤ ንጹሓንም እንዲህ ብለው ያፌዙባቸዋል፤
20
‘በርግጥ ጠላቶቻችን ጠፍተዋል፤ ሀብታቸውም በእሳት ተበልቷል።’
21
“ለእግዚአብሔር ተገዛ፤ ከእርሱም ጋር ሰላም ይኑርህ፤ በረከትም ታገኛለህ።
22
ምክርን ከአፉ ተቀበል፤ ቃሉንም በልብህ አኑር።
23
ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ ትጠገናለህ፤ ክፋትን ከድንኳንህ ብታርቅ፣
24
የወርቅህን አንኳር ትቢያ ላይ፣ የኦፊር ወርቅህንም ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ ብትጥለው፣
25
ሁሉን ቻዩ አምላክ ወርቅ ይሆንልሃል፤ ምርጥ ብር ይሆንልሃል።
26
በዚያ ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፤ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታቀናለህ።
27
ወደ እርሱ ትጸልያለህ፤ እርሱም ይሰማሃል፤ አንተም ስእለትህን ትሰጣለህ።
28
ያሰብኸው ይከናወንልሃል፤ በመንገድህም ላይ ብርሃን ይበራል።
29
ሰዎች ቢዋረዱና አንተ፣ ‘ከፍ አድርጋቸው’ ብትል፣ እርሱ ዝቅ ያሉትን ያድናል፤
30
በጎ ያልሆነውን ሰው እንኳ፣ ከአንተ እጅ ንጽሕና የተነሣ ያድነዋል።”
← Chapter 21
Chapter 23 →