bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Isaiah 18
Isaiah 18
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
በኢትዮጵያ ወንዞች ዳር ለምትገኝ፣ ፉር ፉር የሚሉ ክንፎች ላሉባት ምድር ወዮላት!
2
ይህችውም መልእክተኞችን በባሕር፣ ከወንዞች ማዶ በደንገል ጀልባ የምትልክ ናት። እናንት ፈጣን መልእክተኞች ረዣዥምና ቈዳው ወደ ለሰለሰ፣ ከቅርብም ከሩቅም ወደሚፈራ ሕዝብ፣ ኀያልና ቋንቋው ወደማይገባ፣ ወንዞች ምድሩን ወደሚከፍሉት መንግሥት፣ ሂዱ!
3
እናንት የዓለም ሕዝቦች፣ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፣ በተራሮች ላይ ምልክት ሲሰቀል ታዩታላችሁ፤ መለከትም ሲነፋ ትሰሙታላችሁ።
4
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤ “ጸጥ ብዬ እቀመጣለሁ፤ ከማደሪያዬም በፀሓይ ሐሩር እንደሚያስፈልጋችሁ ብርቅርቅ ትኵሳት፣ በመከርም ሙቀት እንደ ደመና ጠል ሆኜ እመለከታለሁ።”
5
ከመከር በፊት የአበባው ወቅት ሲያልፍ፣ አበባው የጐመራ የወይን ፍሬ ሲሆን፣ የወይን ሐረጉን ተቀጥላ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ የተንሰራፋውንም ቅርንጫፍ ቈራርጦ ያስወግደዋልና።
6
ሁሉም በተራራ ላይ ለሚኖሩ ነጣቂ አሞሮች፣ ለዱርም አራዊት ይተዋሉ፤ አሞሮች በጋውን ሁሉ ሲበሉት ይባጃሉ፤ የዱር አራዊትም ክረምቱን ሁሉ ሲበሉት ይከርማሉ።
7
በዚያን ጊዜ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ፣ ረዣዥምና ቈዳው ከለሰለሰ፣ ከቅርብም ከሩቅም ከሚፈራ ሕዝብ፣ ኀያልና ቋንቋው ከማይገባ፣ ወንዞችም ምድሩን ከሚከፍሉት መንግሥት፣ ገጸ በረከት ይመጣለታል፤ ገጸ በረከቱም የሚመጣለት የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ ነው።
← Chapter 17
Chapter 19 →