bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Isaiah 17
Isaiah 17
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ስለ ደማስቆ የተነገረ ንግር፤ “እነሆ፤ ደማስቆ ከእንግዲህ ከተማነቷ ይቀራል፤ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።
2
የአሮኤር ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ የመንጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።
3
የተመሸገ ከተማ ከኤፍሬም፣ የመንግሥት ሥልጣን ከደማስቆ ይወርዳል፤ የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤላውያን ክብር ይሆናል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ።
4
“በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይደበዝዛል፤ የሰውነቱም ውፍረት ይሟሽሻል።
5
ዐጫጅ የቆመውን ሰብል ሰብስቦ፣ ዛላውንም በክንዱ እንደሚያጭድ፣ ይህም በራፋይም ሸለቆ እንደሚለቀም ቃርሚያ ይሆናል።
6
ሆኖም የወይራ ዛፍ ሲመታ፣ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በቅርንጫፍ ራስ ላይ እንደሚቀር፣ አራት ወይም አምስት ፍሬ ችፍግ ባለው ቅርንጫፍ ላይ እንደሚቀር፣ እንዲሁ ጥቂት ቃርሚያ ይተርፋል” ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ።
7
በዚያ ቀን ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸው ይመለከታሉ፤ ዐይኖቻቸውም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።
8
በእጃቸውም ወደ ሠሯቸው መሠዊያዎች አይመለከቱም፤ በጣቶቻቸው ላበጇቸው የዕጣን መሠዊያዎች፣ ለአሼራም የአምልኮ ዐምዶች ክብር አይሰጡም።
9
በዚያን ቀን በእስራኤል ልጆች ምክንያት የተተዉት ጠንካራ ከተሞች ጥሻና ውድማ እንደ ሆኑ ሁሉ፣ እነዚህ ሁሉ ባድማ ይሆናሉ።
10
አዳኝ አምላክህን ረስተሃል፤ መሸሸጊያ ዐለትህንም አላስታወስህም፤ ስለዚህ ምርጥ ተክል ብትተክልም፣ እንግዳ ዘርንም ብትዘራ፣
11
በተከልህበት ቀን እንዲበቅል፣ በዘራህበትም ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳ፣ መከሩ በደዌና በማይሽር ሕመም ቀን፣ እንዳልነበረ ይሆናል።
12
አቤት፤ የብዙ ሕዝቦች የቍጣ ድምፅ እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል! አቤት፤ የሰዎች ከፍተኛ ጩኸት እንደ ኀይለኛ ውሃ ያስገመግማል!
13
ሰዎቹ እንደ ኀይለኛ ውሃ ጩኸት ቢያስገመግሙም፣ እርሱ ሲገሥጻቸው፣ በኰረብታ ላይ በነፋስ እንደሚበንን ትቢያ፣ በዐውሎ ነፋስ ፊት እንደሚበተን ገለባ ይበተናሉ።
14
እነሆ፤ ሲመሽ ድንገተኛ ሽብር ሆነ! ከመንጋቱ በፊት ግን አንዳቸውም አልተገኙም። የዘረፉን ዕድል ፈንታ፣ የበዘበዙን ዕጣ ይህ ሆነ።
← Chapter 16
Chapter 18 →