bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Hosea 14
Hosea 14
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እስራኤል ሆይ፤ በኀጢአትህ ምክንያት ስለ ወደቅህ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።
2
የምትሉትን ቃል ይዛችሁ፣ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እንዲህም በሉት፤ “ኀጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን፤ የከንፈራችንንም ፍሬ እንድናቀርብ፣ በምሕረትህ ተቀበለን።
3
አሦር ሊያድነን አይችልም፤ በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤ ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣ ‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤ ድኻ ዐደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።”
4
“እኔ ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ፤ እንዲሁ እወድዳቸዋለሁ፤ ቍጣዬ ከእነርሱ ተመልሷልና።
5
እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤ እንደ ውብ አበባ ያብባል፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም፣ ሥር ይሰድዳል፤
6
ቅርንጫፉ ያድጋል፤ ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባ ይሆናል።
7
ሰዎች እንደ ገና ከጥላው በታች ያርፋሉ፤ እርሱም እንደ እህል ይለመልማል፤ እንደ ወይን ተክል ያብባል፤ ዝናውም እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይወጣል።
8
ኤፍሬም ሆይ፤ ከእንግዲህ ከጣዖት ጋር ምን ጕዳይ አለኝ? የምሰማህና የምጠነቀቅልህ እኔ ነኝ፤ እኔ እንደ ለመለመ የጥድ ዛፍ ነኝ፤ ፍሬያማነትህም ከእኔ የተነሣ ነው።”
9
ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤ አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል። የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።
← Chapter 13