bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Ecclesiastes 11
Ecclesiastes 11
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፤ ከብዙ ቀን በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።
2
ሀብትህን ሰባት ቦታ፣ እንዲያውም ስምንት ቦታ ከፍለህ አስቀምጥ፤ በምድሪቱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።
3
ደመናት ውሃ ካዘሉ፣ በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣ በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል።
4
ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚያይ አያጭድም።
5
የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የእግዚአብሔርን ሥራ ማስተዋል አትችልም።
6
ጧት ላይ ዘርህን ዝራ፤ ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ ይህ ወይም ያ፣ ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣ የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና።
7
ብርሃን መልካም ነው፤ ፀሓይንም ማየት ለዐይን ደስ ያሰኛል።
8
ሰው ምንም ያህል ብዙ ዓመት ቢኖር፣ በእነዚህ ሁሉ ይደሰት፤ ነገር ግን ጨለማዎቹንም ቀናት ያስብ፤ እነርሱ ይበዛሉና፤ የሚመጣውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።
9
አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤ የልብህን መንገድ፣ ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
10
ስለዚህ ጭንቀትን ከልብህ አርቅ፤ ክፉ ነገርንም ከሰውነትህ አስወግድ፤ ወጣትነትና ጕብዝና ከንቱ ናቸውና።
← Chapter 10
Chapter 12 →