bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Ecclesiastes 10
Ecclesiastes 10
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
የሞቱ ዝንቦች ሽቶን እንደሚያገሙ፣ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብንና ክብርን ያቀልላል።
2
የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ፣ የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራ ያዘነብላል።
3
ሞኝ በጐዳና ሲሄድ ማስተዋል ይጐድለዋል፤ ጅል መሆኑንም ለማንም ይገልጻል።
4
የገዥ ቍጣ በተነሣብህ ጊዜ፣ ስፍራህን አትልቀቅ፤ ትዕግሥት ታላቁን ጥፋት ጸጥ ያደርጋልና።
5
ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፤ ይህም ከገዥ የሚወጣ ስሕተት ነው፤
6
ሞኞች በብዙ የክብር ስፍራዎች ሲቀመጡ፣ ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ስፍራ ሆነዋል።
7
መሳፍንት እንደ ባሮች በእግራቸው ሲሄዱ፣ ባሮች ፈረስ ላይ ተቀምጠው አይቻለሁ።
8
ጕድጓድን የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ ቅጥርንም የሚያፈርስ እባብ ይነድፈዋል።
9
ድንጋይ የሚፈነቅል ይጐዳበታል፤ ግንድንም የሚፈልጥ አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም።
10
መጥረቢያ ቢደንዝ፣ ጫፉም ባይሳል፣ ብዙ ጕልበት ይጨርሳል፤ ብልኀት ግን ለውጤት ያበቃል።
11
እባብ በድግምት ከመፍዘዙ በፊት ቢነድፍ፣ ለደጋሚው ምንም አይጠቅመውም።
12
ከጠቢብ አፍ የሚወጣ ቃል ባለ ሞገስ ነው፤ ሞኝ ግን በገዛ ከንፈሩ ይጠፋል፤
13
ቃሉ በመጀመሪያ ሞኝነት ነው፤ በመጨረሻም ደግሞ ክፉ እብደት ነው፤
14
ሞኙም ቃልን ያበዛል። የሚመጣውን የሚያውቅ የለም፤ ከእርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ማን ሊነግረው ይችላል?
15
የሞኝ ሥራ ራሱን ያደክመዋል፤ ወደ ከተማ የሚወስደውንም መንገድ አያውቅም።
16
አንቺ፣ ንጉሥሽ ልጅ የሆነ፣ መሳፍንትሽም በጧት ግብዣ የሚያደርጉ ምድር ሆይ፤ ወዮልሽ!
17
አንቺ ንጉሥሽ ከተከበረው ዘር የሆነ፣ ለመስከር ሳይሆን ለብርታት፣ በተገቢው ጊዜ የሚበሉ መሳፍንት ያሉሽ ምድር ሆይ፤ የተባረክሽ ነሽ፤
18
ሰው ሰነፍ ከሆነ ጣራው ይዘብጣል፤ እጆቹም ካልሠሩ ቤቱ ያፈስሳል።
19
ግብዣ ለሣቅ ያዘጋጃል፤ ወይንም ሕይወትን ያስደስታል፤ ገንዘብም ካለ ሁሉ ነገር አለ።
20
በዐሳብህም እንኳ ንጉሥን አትንቀፍ፤ በመኝታ ክፍልህም ባለጠጋን አትርገም፤ የሰማይ ወፍ ቃልህን ልትወስድ፣ የምትበረዋም ወፍ የምትለውን ልታደርስ ትችላለችና።
← Chapter 9
Chapter 11 →