bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Deuteronomy 6
Deuteronomy 6
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር እንድትጠብቁት አስተምራችሁ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሰጠኝ ትእዛዝ፣ ሥርዐትና ሕግ ይህ ነው፤
2
ይኸውም፣ የምሰጣችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፣ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም፣ አንተ፣ ልጆችህና ከእነርሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቻቸው በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትፈሩት ዘንድ ነው።
3
እንግዲህ እስራኤል ሆይ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት በምታፈስሰው ምድር መልካም እንዲሆንልህና እጅግ እንድትበዛ፣ ትእዛዙንም ትጠብቅ ዘንድ ጥንቃቄ አድርግ።
4
እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አንድ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው ።
5
አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህ ውደድ።
6
ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች በልብህ ያዝ።
7
ለልጆችህም አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።
8
በእጅህ ላይ ምልክት አድርገህ እሰራቸው፤ በግንባርህም ላይ ይሁኑ።
9
በቤትህ መቃኖች በግቢህም በሮች ላይ ጻፋቸው።
10
አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ሲያስገባህ፣ በዚያም ያልሠራሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞችን፣
11
የራስህ ባልነበሩ መልካም ነገሮች ሁሉ የተሞሉ ቤቶችን፣ ያልቈፈርሃቸውን የውሃ ጕድጓዶች፣ ያልተከልሃቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ሲሰጥህና በልተህም ስትጠግብ፣
12
ከባርነት ምድር ከግብፅ ያወጣህን እግዚአብሔርን (ያህዌ) እንዳትረሳ ተጠንቀቅ!
13
አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ፍራ፤ እርሱን ብቻ አገልግል፤ በስሙም ማል።
14
በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን ሌሎች አማልክት አትከተል፤
15
ምክንያቱም በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ቀናተኛ አምላክ (ኤሎሂም) ስለሆነ፣ በአንተም ላይ ቍጣው ስለሚነድድ፣ ከምድር ገጽ ያጠፋሃል።
16
በማሳህ እንዳደረጋችሁት አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) አትፈታተኑት።
17
አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሰጣችሁን ትእዛዞች፣ መመሪያዎችና ሥርዐቶች በጥንቃቄ ጠብቁ።
18
መልካም እንዲሆንልህና እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአባቶችህ በመሐላ እንድትወርሳት፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ተስፋ የሰጣቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ ቀናና መልካም የሆነውን አድርግ፤
19
እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረትም ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ታስወጣለህ።
20
በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፣ “አምላካችን እግዚአብሔር (ያህዌ ኤሎሂም) ያዘዛችሁ የመመሪያዎቹ፣ የሥርዐቶቹና የሕጎቹ ትርጕም ምንድን ነው?” ብሎ በሚጠይቅህ ጊዜ፣
21
እንዲህ በለው፤ “እኛ በግብፅ የፈርዖን ባሮች ነበርን፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን በብርቱ እጅ ከግብፅ አወጣን።
22
እኛ በዐይናችን እያየን እግዚአብሔር (ያህዌ) ታላላቅና አስፈሪ የሆኑ ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆችን በግብፅ፣ በፈርዖንና በመላው ቤተ ሰዎቹ ላይ አደረገ።
23
እኛን ግን ለአባቶቻችን በመሐላ ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ሊያስገባንና ሊሰጠን ከዚያ አወጣን።
24
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ምንጊዜም መልካም እንዲሆንልንና በሕይወት እንድንኖር ይህን ሥርዐት ሁሉ እንድንፈጽም፣ አምላካችንንም እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) እንድንፈራ እግዚአብሔር (ያህዌ) አዘዘን።
25
እንግዲህ ይህን ሁሉ ሕግ እርሱ ባዘዘን መሠረት፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ተጠንቅቀን ከጠበቅን፣ ያ ለእኛ ጽድቃችን ይሆናል።”
← Chapter 5
Chapter 7 →