bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
1 Chronicles 11
1 Chronicles 11
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እስራኤል ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉት፤ “እነሆ፤ እኛ የገዛ ሥጋህና ደምህ ነን፤
2
በቀደመው ዘመን ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን ወደ ጦርነት የምትመራ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔር አምላክህም፣ ‘ሕዝቤን እስራኤልን የምትጠብቅ አንተ ነህ፤ ንጉሣቸውም ትሆናለህ’ ብሎሃል”።
3
የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባ። እግዚአብሔር በሳሙኤል አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።
4
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ ኢያቡስ ወደምትባለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ። በዚያም የሚኖሩ ኢያቡሳውያን
5
ዳዊትን፣ “ወደዚህ ፈጽሞ አትገባም” አሉት፤ ዳዊት ግን የጽዮንን ምሽግ ያዘ፤ እርሷም የዳዊት ከተማ ናት።
6
ዳዊትም፣ “ኢያቡሳውያንን ቀድሞ የሚወጋ ሰው የሰራዊቱ አዛዥ ይሆናል” አለ፤ ስለዚህ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ወጣ፤ እርሱም አዛዥ ለመሆን በቃ።
7
ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐምባዪቱ ውስጥ አደረገ፤ ከዚህም የተነሣ የዳዊት ከተማ ተባለች።
8
ዳዊትም ከሚሎ ጀምሮ የከተማዪቱን ዙሪያ ቅጥር ሠራ፤ ኢዮአብ ደግሞ የቀረውን የከተማዪቱን ክፍል መልሶ ሠራ።
9
እግዚአብሔር ጸባኦት ከእርሱ ጋር ስለ ነበር፣ ዳዊት በየጊዜው እየበረታ ሄደ።
10
የዳዊት ኀያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱ በምድሪቱ ሁሉ ትሰፋ ዘንድ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።
11
የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም ዝርዝር ይህ ነው፤ ሐክሞናዊው ያሾብዓም የጦር መኮንኖቹ አለቃ ነበረ፤ እርሱም ጦሩን አንሥቶ በአንድ ጊዜ ሦስት መቶ ሰው ገደለ።
12
ከእርሱም ቀጥሎ ከሦስቱ ኀያላን አንዱ የሆነው የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ አልዓዛር ነው፤
13
እርሱም ፍልስጥኤማውያን ለጦርነት በተሰበሰቡ ጊዜ በፈስደሚም ከዳዊት ጋር አብሮ ነበረ፤ ገብስ በሞላበት የዕርሻ ቦታ ወታደሮቹ ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤
14
ይሁን እንጂ በዕርሻው መካከል ቦታ ይዘው ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤ እግዚአብሔርም ታላቅ ድል ሰጣቸው።
15
ከፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ጥቂቱ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ ከሠላሳዎቹ አለቆች ሦስቱ ዳዊትን ለመገናኘት በዓዶላም ዋሻ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ዐለቱ ወረዱ።
16
በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ደግሞ በቤተ ልሔም ነበረ።
17
ዳዊትም ውሃ ፈልጎ ነበርና፣ “ከቤተ ልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው ጕድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ።
18
በዚህ ጊዜ ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ጥሰው በማለፍ በቤተ ልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጕድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው።
19
ከዚያም፣ “ይህን ከማድረግ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ፤ ይህ በሕይወታቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ መጠጣት አይደለምን?” አለ። ይህን ለማምጣት በሕይወታቸው ቈርጠው ስለ ነበር፣ ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱ ኀያላን ሰዎች የሠሩት ይህን ነበር።
20
የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ።
21
ከሦስቱ አንዱ ሆኖ ባይቈጠርም እንኳ፣ ዕጥፍ ክብር አገኘ፤ አዛዣቸውም ሆነ።
22
ከቀብስኤል የመጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠራው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ። እርሱም እጅግ የታወቁ ሁለት የሞአብ ሰዎችን ገደለ። እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሸፈነበት ቀን ወደ አንድ ጕድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።
23
ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብፃዊ ገደለ፤ ግብፃዊው የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር በእጁ ቢይዝም፣ በናያስ ግን ቈመጥ ይዞ ገጠመው፤ ከግብፃዊው እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።
24
የዮዳሄ ልጅ በናያስ የፈጸመው ጀብዱ ይህ ነበር፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ዝነኛ ሆነ።
25
ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ ክብር ተጐናጸፈ፤ ይሁን እንጂ ከሦስቱ አንዱ አልነበረም፤ ዳዊትም የክብር ዘቡ አዣዥ አደረገው።
26
ኀያላኑም እነዚህ ነበሩ፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣ የቤተ ልሔሙ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣
27
ሃሮራዊው ሳሞት፣ ፊሎናዊው ሴሌድ፣
28
የቴቍሔ ሰው የሆነው የዒስካ ልጅ፣ ዒራስ፣ የዓናቶቱ ሰው አቢዔዜር፣
29
ኩሳታዊው ሴቤካይ፣ አሆሃዊው ዔላይ፣
30
ነጦፋዊው ማህራይ፣ የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፣
31
ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኤታይ፣ ጲርዓቶናዊው በናያስ፣
32
የገዓስ ሸለቆዎች ሰው የሆነው ኡሪ፣ ዐረባዊው አቢኤል፣
33
ባሕሩማዊው ዓዝሞት፣ ሰዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣
34
የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፣ የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣
35
የሃራራዊው የሳኮር ልጅ አሒአም፣ የኡር ልጅ ኤሊፋል፣
36
ምኬራታዊው ኦፌር፣ ፍሎናዊው አኪያ፣
37
ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣ የኤዝባይ ልጅ ነዕራይ፤
38
የናታን ወንድም ኢዮኤል፣ የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፣
39
አሞናዊው ጼሌቅ፣ የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮታዊው ነሃራይ፣
40
ይትራዊው ዒራስ፣ ይትራዊው ጋሬብ፣
41
ኬጢያዊው ኦርዮ፣ የአሕላይ ልጅ ዛባድ፣
42
የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ ዓዲና፤ እርሱም የሮቤላውያንና አብረውት ለነበሩት የሠላሳ ሰዎች አለቃ ነበረ።
43
የማዕካ ልጅ ሐናን፣ ሚትናዊው ኢዮሣፍጥ፣
44
አስታሮታዊው ዖዝያ፣ የአሮዔራዊው የኮታም ልጆች ሻማና ይዒኤል፣
45
የሺምሪ ልጅ ይዲኤል፣ ወንድሙም ቴዳዊው ዮሐ፣
46
መሐዋዊው ኤሊኤል፣ የኤልነዓም ልጆች ይሪባይና ዮሻውያ፣ ሞዓባዊው ይትማ፣
47
ኤሊኤል፣ ዖቤድና ምጾባዊው የዕሢኤል።
← Chapter 10
Chapter 12 →