bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
1 Chronicles 10
1 Chronicles 10
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን መውጋት ጀመሩ፤ እስራኤላውያንም ከፊታቸው ሸሹ፤ ብዙዎች በጊልቦዓ ተራራ ላይ ሞቱ።
2
ፍልስጥኤማውያን ሳኦልንና ልጆቹን ይበልጥ አሳደዷቸው፤ የሳኦልንም ልጆች ዮናታንን፣ አሚናዳብንና ሜልኪሳን ገደሉ፤
3
ሳኦል በተሰለፈበት ግንባር ውጊያው በረታ፤ ቀስተኞችም አግኝተው አቈሰሉት።
4
ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን፣ “እነዚህ ሸለፈታሞች መሳለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር አልደፈረም፤ ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
5
ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ሲያይ፣ እርሱም በሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
6
ስለዚህ ሳዖልና ሦስት ልጆቹ ሞቱ፤ ቤተ ሰዎቹም ሁሉ አብረው ሞቱ።
7
በሸለቆው ውስጥ የነበሩት እስራኤላውያን ሁሉ ሰራዊቱ እንደ ሸሸ፣ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ከተሞቹን ያዙ።
8
በማግስቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ ሲመጡ፣ ሳኦልና ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።
9
ሳኦልን ከገፈፉ፣ ራሱን ከቈረጡና መሣሪያውንም ከወሰዱ በኋላ፣ ለአማልክቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲነግሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክተኞችን ላኩ።
10
ከዚያም መሣሪያውን በአማልክታቸው ቤተ ጣዖት አኖሩ፤ ራሱንም በዳጎን ቤተ ጣዖት ውስጥ አንጠለጠሉት።
11
የኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ፣
12
ብርቱ የሆኑ ሰዎች ሄደው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ አንሥተው ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ከዚያም ሰባት ቀን ጾሙ።
13
ሳኦል እግዚአብሔርን ስላልታዘዘ ሞተ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልጠበቀም፤ ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤
14
ይህን ከእግዚአብሔር አልጠየቀም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።
← Chapter 9
Chapter 11 →