bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 99
Psalms 99
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ጌታ ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፥ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።
2
ጌታ በጽዮን ታላቅ ነው፥ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።
3
ቅዱስ ነውና ሁሉም ታላቅና ግሩም ስምህን ያመስግኑ።
4
ፍርድን የምትወድ ኃያል ንጉሥ፥ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ በያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ ፈጽምህ።
5
ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መርገጫ ስገዱ።
6
ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው፥ ጌታን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።
7
በደመና ዓምድም ተናገራቸው፥ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።
8
አቤቱ አምላክችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፥ አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥ ጥፋታቸውን ሁሉ ግን ተበቀልሃቸው።
9
ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፥ ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
← Chapter 98
Chapter 100 →