bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 83
Psalms 83
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
2
አቤቱ፥ በጸጥታ አትቆይ፥ አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።
3
እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።
4
ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።
5
ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።
6
በአንድ ልብ በአንተ ላይ ተማከሩ፥ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፥
7
የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥
8
ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፥
9
አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኗቸው።
10
እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥ በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው።
11
በዓይንዶር ጠፉ፥ እንደ ምድርም ጉድፍ ሆኑ።
12
አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥ ታላላቆቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፦
13
የእግዚአብሔርን መስክ እንወርሳለን የሚሉትን።
14
አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው።
15
እሳት ደንን እንደሚያቃጥል፥ ነበልባልም ተራሮችን እንደሚያነድድ፥
16
እንዲሁ በቁጣህ አሳድዳቸው፥ በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው።
17
ፊታቸውን እፍረት ሙላው፥ አቤቱ፥ ስምህንም ይፈልጋሉ።
18
ይፈሩ ለዘለዓለሙም ይታወኩ፥ ይጐስቁሉ ይጥፉም።
19
ስምህም “ጌታ” እንደሆነ፥ በምድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደሆንህ ይወቁ።
← Chapter 82
Chapter 84 →