bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 82
Psalms 82
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የአሳፍ መዝሙር። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጉባኤ ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።
2
እስከ መቼ ሐሰትን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼስ ለክፉዎች ታደላላችሁ?
3
ለድሆችና ወላጅ ለሞተባቸው ፍረዱ፥ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ፍትሕን አድርጉ፥
4
ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፥ ከክፉዎችም እጅ አስጥሉአቸው።
5
አያውቁም፥ አያስተውሉም፥ በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፥ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።
6
እኔ ግን፦ አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ አልሁ፥
7
ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ።
8
አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍረድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።
← Chapter 81
Chapter 83 →