bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 59
Psalms 59
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ሳኦል ይገድሉት ዘንድ ቤቱን እንዲጠብቁ በላከ ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
2
አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶቼ አድነኝ፥ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ።
3
ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ።
4
እነሆ፥ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፥ ብርቱዎችም በላዬ ተሰበሰቡ፥ አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኃጢአቴም አይደለም።
5
ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፥ ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም።
6
አንተም አቤቱ፥ የኃያላን አምላክ፥ የእስራኤል አምላክ፥ አሕዛብን ሁሉ ትጐበኛቸው ዘንድ ተነሥ፥ ክፉ ከዳተኞችን ሁሉ አትማራቸው።
7
ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ያላዝኑ፥ በከተማም ይዙሩ።
8
እነሆ፥ በአፋቸው ግሳት ይናገራሉ፥ ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፥ ማን ይሰማል? ይላሉ።
9
አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛብንም ሁሉ ማላገጫ ታደርጋቸዋለህ።
10
እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና ኃይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ።
11
የአምላኬ ቸርነቱ ይገናኘኛል አምላኬ በጠላቶቼ ላይ ያሳየኛል።
12
ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።
13
ስለ አፋቸው ኃጢአት ስለ ከንፈራቸውም ቃል፥ መርገምንና ሐሰትን ስለሚናገሩ፥ በትዕቢታቸው ይጠመዱ።
14
በቁጣ አጥፋቸው፥ እንዳይኖሩም አጥፋቸው፥ የያዕቆብም አምላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንደሚገዛ ይወቁ።
15
ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።
16
እነርሱም መብል ለመፈለግ ይበተኑ፥ ያልጠገቡ እንደሆነም ያላዝኑ።
17
እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ፥ በምሕረትህም ማልዶ ደስ ይለኛል፥ በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኸኛልና።
18
ረዳቴ ሆይ፥ ለአንተ ለአምላኬ እዘምራለሁ፥ አንተ፥ አምላኬ፥ መጠጊያዬ የቸርነትም አምላኬ ነህና።
← Chapter 58
Chapter 60 →