bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 58
Psalms 58
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የዳዊት ቅኔ።
2
በእውነት ጽድቅን ትናገራላችሁን፥ ገዢዎች ሆይ፥ በቅን ትፈርዳላችሁን?
3
በልባችሁ በምድር ላይ ግፍን ትሠራላችሁና፥ እጆቻችሁም ዐመጽን ይፈጽማሉና።
4
ክፉዎች ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፥ ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ።
5
የእባብ መርዝ ዓይነት መርዝ አላቸው፥ ጆሮውን እንደደፈነ እባብ ናቸው፥
6
አስማተኛ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ።
7
አምላክ ሆይ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፥ የአንበሶቹን መንጋጋቸውን አድቅቅ።
8
እንደሚፈስስ ውኃ ይጥፉ፥ ቀስትን ሲገትሩ ፍላጻው ይጣመም።
9
እንደሚሟሟ ቀንድ አውጣ፥ ፀሐይን እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ።
10
ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።
11
ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፥ በክፉዉም ደም እግሮቹን ይታጠባል።
12
ሰውም፦ “በእውነት ለጻድቅ ፍሬ አለው፥ በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላል።
← Chapter 57
Chapter 59 →