bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 53
Psalms 53
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ በማኽላት፥ የዳዊት ትምህርት።
2
ኣላዋቂ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፥ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።
3
የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
4
ሁሉም በደሉ፥ አብረውም ረከሱ፥ አንድ እንኳ በጎን ነገር የሚያደርጋት የለም።
5
እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉ ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
6
በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅጉን ፈሩ፥ እግዚአብሔር የከበቡህን አጥንቶች በትኖአልና፥ እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና አሳፈርሃቸው።
7
መድኃኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን በሰጠ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።
← Chapter 52
Chapter 54 →