bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 41
Psalms 41
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2
ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፥ ጌታ በክፉ ቀን ያድነዋል።
3
ጌታ ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ብፁዕ ያደርጋቸዋል፥ ለጠላቶቹም አሳልፈህ አትሰጠውም።
4
ጌታ በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፥ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።
5
እኔስ፦ “አቤቱ፥ ማረኝ፥ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።
6
ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦ መቼ ይሞታል ስሙስ መቼ ይሻራል? ይላሉ።
7
እኔን ለመጠየቅ የሚገባ ከንቱን ይናገራል፥ ልቡ ኃጢአትን ሰበሰበለት፥ ወደ ውጭ ይወጣል ይናገራልም።
8
በላዬ በመተባበር ጠላቶቼ ሁሉ ያንሾካሽካሉ፥ በእኔ ላይም ክፋትን ያስባሉ።
9
ክፉ ነገር መጣበት፥ ከተኛበት ከእንግዲህ ወዲህ አይነሣም ይላሉ።
10
ደግሞ የሰላሜ ሰው፥ የታመንሁበት እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።
11
አንተ ግን አቤቱ፥ ማረኝ፥ እመልስላቸውም ዘንድ አቁመኝ።
12
ጠላቴ እልል አይልብኝምና በዚህም በእኔ እንደ ተደሰትክ አወቅሁ።
13
እኔንም ስለ ቅንነቴ ደገፍከኝ፥ በፊትህም ለዘለዓለም አጸናኸኝ።
14
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ። አሜን አሜን።
← Chapter 40
Chapter 42 →