bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 40
Psalms 40
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2
በትዕግሥት ጌታን ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኸቴንም ሰማኝ።
3
ከጥፋት ጉድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።
4
አዲስ ዝማሬን ለአምላካችን ምስጋና በአፌ ጨመረ፥ ብዙዎች ያያሉ ይፈሩማል፥ በጌታም ይታመናሉ።
5
ጌታን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።
6
አቤቱ አምላኬ፥ ያደረግኸው ተአምራት ብዙ ነው፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፥ ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ።
7
መሥዋዕትንና ቁርባንን አልወደድህም፥ የሚሰማ ጆሮ ሰጠኸኝ፥ የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልፈለግህም።
8
በዚያን ጊዜ እንዲህ አልሁ፦ “እነሆ፥ መጣሁ፥ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፥
9
አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”
10
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አበሠርሁ፥ እነሆ፥ ከንፈሮቼን አላግድም፥ አቤቱ፥ አንተ ታውቃለህ።
11
አዳኝ ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሰወርኩም፥ ታማኝነትህንና ማዳንህንም ተናገርሁ፥ ጽኑ ፍቅርህንና እውነትህን ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።
12
አቤቱ፥ አንተ ርኅራኄህን ከእኔ አታርቅ፥ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።
13
ቍጥር የሌለው ክፋት ከቦኛልና፥ ኃጢአቶቼ ያዙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል ከራሴ ጠጉር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
14
አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፥ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
15
ነፍሴን ለማጥፋት የሚወድዱ ይፈሩ፥ በአንድነትም ይዋረዱ፥ በእኔ ላይ ክፋትን ሊያደርጉ የሚወድዱ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይጐስቁሉም።
16
እሰይ እሰይ የሚሉኝ እፍረታቸውን ወዲያው ይከፈሉ።
17
አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፥ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ ዘወትር፦ ጌታ ታላቅ ይሁን ይበሉ።
18
እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ ጌታ ግን ያስብልኛል፥ አንተ ረዳቴና አዳኜ ነህ፥ አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ።
← Chapter 39
Chapter 41 →