bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 30
Psalms 30
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለቤቱ መመረቅ ምስጋና፥ የዳዊት መዝሙር።
2
አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ ጠላቶቼንም ደስ አላሰኘህብኝምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።
3
አቤቱ አምላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ አንተም ፈወስከኝ።
4
አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጉድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።
5
ቅዱሳን ሆይ፥ ለጌታ ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።
6
ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፥ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፥ ልቅሶ ማታ ይመጣል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
7
እኔም በደስታዬ፦ ለዘለዓለም አልታወክም አልሁ።
8
አቤቱ፥ በፈቃድህ እንደ ጽኑ ተራራ አጠነከርከኝ፥ ፊትህን ስትሰውር፥ እኔም ደነገጥሁ።
9
አቤቱ፥ ወደ አንተ ጠራሁ፥ ወደ አምላኬም ለመንሁ።
10
ወደ ጉድጓድ ብወርድ ከደሜ ምን ጥቅም ይገኛል? አፈር ያመሰግንሃልን? እውነትህንም ይናገራልን?
11
ጌታ ሰማ ማረኝም፥ ጌታ ረዳቴ ሆነኝ።
12
ልቅሶዬን ወደ እልልታ ለወጥህልኝ፥ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ።
13
ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል፥ አቤቱ አምላኬ፥ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።
← Chapter 29
Chapter 31 →