bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 29
Psalms 29
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ከድንኳን በሚወጣበት ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር። የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለጌታ አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለጌታ አምጡ።
2
የስሙን ክብር ለጌታ አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ።
3
የጌታ ድምፅ በውኆች ላይ፥ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥ አምላክ በብዙ ውኆች ላይ።
4
የጌታ ድምፅ በኃይል ነው፥ የጌታ ድምፅ በታላቅ ክብር የተሞላ ነው።
5
የጌታ ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፥ ጌታ የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
6
እንደ ጥጃ ሊባኖስን ፥ እንደ ጎሽ ጥጃ ስርዮንን ያዘልላቸዋል።
7
የጌታ ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
8
የጌታ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ ጌታ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9
የጌታ ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ጫካዎቹንም ይገልጣል፥ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
10
ጌታ የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፥ ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
11
ጌታ ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፥ ጌታ ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።
← Chapter 28
Chapter 30 →