bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 102
Psalms 102
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ባዘነና ልመናውን በጌታ ፊት ባፈሰሰ ጊዜ የችግረኛ ጸሎት።
2
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ።
3
በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ።
4
ዘመኔ እንደ ጢስ አልቃለችና፥ አጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ተቃጥለዋልና።
5
ልቤም እንደ ተመታ ሣር ደረቀ፤ እህል መብላትም ተረሳኝ።
6
ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ አጥንቶቼ ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ።
7
እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፥ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጉጉት ሆንሁ።
8
ነቅቼ፥ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁ።
9
ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም በእኔ ስም ይራገማሉ።
10
አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና፥ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና፥
11
ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ፥ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና።
12
ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፥ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።
13
አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘለዓለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው።
14
አንተ ተነሥ ለጽዮንም ራራ፥ የጸጋዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና፥
15
አገልጋዮችህ ድንጋዮችዋን ወድደዋልና፥ ለመሬትዋም አዝነዋልና።
16
አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፥
17
ጌታ ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና።
18
ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም።
19
ይህ ለሚመጣ ትውልድ ይጻፍ፥ የሚፈጠርም ሕዝብ ለጌታ እልል ይላል፥
20
ጌታ ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ከሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና፥
21
የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥ ሊገድሉ የተፈረደባቸውን ይፈታ ዘንድ፥
22
የጌታን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ፥
23
አሕዛብ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ መንግሥታትም ለጌታ ይገዙ ዘንድ።
24
በመንገዴ ጉልበቴ ዛለ፦ ዘመኔም አጠረ።
25
ለእኔም ንገረኝ፥ በዘመኔ እኩሌታ አትውሰደኝ፥ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው።
26
አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።
27
እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፥ ሁላቸውም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጣሉም፥
28
አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።
29
የአገልጋዮችህ ልጆች ይኖራሉ፥ ዘራቸውም በፊትህ ትጸናለች።
← Chapter 101
Chapter 103 →