bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 101
Psalms 101
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ።
2
ነቀፋ በሌለበት መንገድን እጓዛለሁ፥ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ? በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ።
3
በዓይኔ ፊት ክፉን ነገር አላኖርሁም፥ ሕግ ተላላፊዎችን ጠላሁ።
4
ጠማማ ልብም ከእኔ ይርቃል፥ ክፉን አላውቀውም።
5
ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፥ በዓይኑ ትዕቢተኛ፥ በልቡ ኩራተኛ የሆነውን አልታገሥም።
6
ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ ዐይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው፥ በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል።
7
አታላይ በቤቴ መካከል አይኖርም፥ ሐሰትን የሚናገር በዓይኔ ፊት አይቆምም።
8
ዓመፃ የሚያደርጉትን ሁሉ ከጌታ ከተማ አጠፋቸው ዘንድ፥ የምድርን ክፉዎች ሁሉ በማለዳ አጠፋቸዋለሁ።
← Chapter 100
Chapter 102 →