bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Job 22
Job 22
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2
“በውኑ ሰው እግዚአብሔርን ይጠቅመዋልን? ይልቁንም ጥበበኛ ሰው ራሱን ይጠቅማል።
3
ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን? መንገድህን ማቅናትህስ ይጠቅመዋልን?
4
እርሱንስ ስለ ፈራህ ይዘልፍሃልን? ወደ ፍርድስ ከአንተ ጋር ይገባልን?
5
ክፋትህስ ብዙ አይደለምን? ለዐመፅህም ወሰን የለውም።
6
ከወንድሞችህ አላግባብ መያዣ ወስደሃል፥ የታረዙትንም ልብስ ዘርፈሃል።
7
በጥም የደከመውን ውኃ አላጠጣህም፥ የተራበውንም እንጀራ ከልክለሃል።
8
ኃይለኛ ሰው መሬት ገዛ፥ የተከበረ ሰው ተቀመጠባት።
9
መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰድደሃቸዋል፥ የወላጅ አልቦችም ክንዶች ተሰብረዋል።
10
ስለዚህ ወጥመዶች ከብበውሃል፥ ድንገተኛ ፍርሃትም አናውጦሃል።
11
እንዳታይ ብርሃን ጨለማ ሆነችብህ፥ የውኆችም ሙላት አሰጠመህ።”
12
“እግዚአብሔር በላይ በሰማያት አይደለምን? ከዋክብትም እንዴት ከፍ ባለ ስፍራ ላይ እንዳሉ ተመልከት።”
13
አንተም፦ “እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን?
14
እንዳያይ የጠቈረ ደመና ጋርዶታል፥ በሰማይ ክበብ ላይ ይራመዳል” ብለሃል።
15
“በውኑ ክፉ ሰዎች የሄዱበትን የዱሮውን መንገድ ትከተላለህን?
16
ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፥ መሠረታቸውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።”
17
እነርሱም እግዚአብሔርን፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ምን ሊያደርግልን ይችላል?” አሉት።
18
“ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞልቶት ነበር፥ የክፉ ሰው ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት።
19
ይህንን አይተው ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፥ ንጹሑም ሰው ይስቅባቸዋል።
20
በእውነት ጠላቶቻችን ጠፍተዋል፥ ከንብረታቸው የተረፈውንም እሳት በላች።”
21
“እንግዲህ አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፥ በዚያም መልካምን ታገኛለህ።
22
ከአፉም ትምህርቱን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፥
23
ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ ትደረጃለህ ፥ ክፋትንም ከድንኳንህ ብታርቅ፥
24
ወርቅን በአፈር ውስጥ ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥
25
ሁሉን የሚችል አምላክ ወርቅና የሚብለጨለጭ ብር ይሆንልሃል።
26
የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።
27
ወደ እርሱም ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፥ ስእለትህንም ትሰጣለህ።
28
በጉዳዮችም ላይ ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል፥ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።
29
ቢያዋርዱ፥ አንተ ‘መነሣት አለ’ ትላለህ፥ ትሑቱንም ሰው ያድነዋል።
30
ንጹሑን ሰው ያድነዋል፥ በእጅህም ንጽሕና ትድናለህ።”
← Chapter 21
Chapter 23 →