bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 56
Psalms 56
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ይቅር በለኝ፥ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፤ ኀጢአት እስክታልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።
2
ወደ ልዑል እግዚአብሔር፥ ወደሚረዳኝ እግዚአብሔር እጮኻለሁ።
3
ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና ጽድቁን ላከ።
4
ነፍሴን ከአንበሶች መካከል አዳናት። ደንግጬም ተኛሁ፤ የሰው ልጆች ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ ነው፥ አንደበታቸውም የተሳለ ሾተል ነው።
5
እግዚአብሔር በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብሩም በምድር ሁሉ ላይ ነው።
6
ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥ ሰውነቴንም አጐበጡአት፤ ጕድጓድን በፊቴ ቈፈሩ፥ በውስጡም ወደቁ።
7
ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አመሰግናለሁ፥ እዘምራለሁም።
8
ክብሬ ይነሣ፥ በበገናና በመሰንቆ ይነሣ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
9
አቤቱ፥ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ በወገኖችም ዘንድ እዘምርልሃለሁ፤
10
ምሕረትህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና፥ ጽድቅህም እስከ ደመናት ድረስ።
11
እግዚአብሔር በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብሩም በምድር ሁሉ ላይ ነው።
← Chapter 55
Chapter 57 →