bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 55
Psalms 55
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ሰው ረግጦኛልና ይቅር በለኝ፤ ሁልጊዜም ሰልፍ አስጨንቆኛል።
2
ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ጠላቶች ረገጡኝ፥ የሚዋጉኝ በዝተዋልና ፈራሁ።
3
እኔ ግን አቤቱ በአንተ ታመንሁ።
4
በእግዚአብሔር ቃሉን አከብራለሁ፤ በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?
5
ሁልጊዜ ቃሎችን ይጸየፉብኛል፤ በእኔ ላይም የሚመክሩት ሁሉ ለክፉ ነው።
6
ይሸምቁብኛል፥ ይሸሸጉኝማል፥ እነርሱም ተረከዜን ይመለካከታሉ፥ ሁልጊዜም ነፍሴን ይሸምቁባታል።
7
በምንም ምን አታድናቸውም፤ አሕዛብን በመዓትህ ትጥላቸዋለህ።
8
አምላኬ ሆይ፥ ሕይወቴን እነግርሃለሁ፤ እንባዬንም እንደ ትእዛዝህ በፊትህ አኖርሁ።
9
በጠራሁህ ጊዜ ጠላቶች ወደ ኋላቸው ይመለሱ፤ አንተ አምላኬ እንደ ሆንህ እነሆ፥ ዐወቅሁ።
10
በእግዚአብሔር ቃሌን አከብራለሁ፤ የተናገርሁትም በእግዚአብሔር ዘንድ ይከብራል።
11
በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?
12
አቤቱ፥ የምስጋና ስእለት የምሰጥህ ከእኔ ዘንድ ነው፤
13
ነፍሴን ከሞት፥ ዐይኖቼን ከዕንባ፥ እግሮቼንም ከድጥ አድነሃልና፥ በሕያዋን ሀገር እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ።
← Chapter 54
Chapter 56 →