bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 51
Psalms 51
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ኀያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትኰራለህ? ሁልጊዜስ ለምን ትበድላለህ?
2
ልብህ ኀጢአትን ያስባል፤ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ።
3
ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ።
4
የሚያሰጥም የምላስ ነገርን ሁሉ ወደድህ።
5
ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፤ ከቤትህም ይነቅልሃል፥ ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
6
ጻድቃን አይተው ይፍሩ፤ በእርሱም ይሳቁ እንዲህም ይበሉ፦
7
“እግዚአብሔርን ረዳቱ ያላደረገ፥ በባለጠግነቱም ብዛት የታመነ፥ በከንቱ ነገርም የበረታ ያ ሰው እነሆ።”
8
እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤ ለዓለምና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ምሕረት ታመንሁ።
9
አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፥ በጻድቃንህም ዘንድ መልካም ነውና ምሕረትህን ተስፋ አደርጋለሁ።
← Chapter 50
Chapter 52 →