bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 50
Psalms 50
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት ኀጢአቴን ደምስስ።
2
ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኀጢአቴም አንጻኝ፤
3
እኔ በደሌን አውቃለሁና፥ ኀጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።
4
አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ።
5
እነሆ፥ በኀጢአት ተፀነስሁ፥ እናቴም በዐመፃ ወለደችኝ።
6
እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይነገር ስውር ጥበብህን አስታወቅኸኝ።
7
በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።
8
ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የጻድቃን አጥንቶች ደስ ይላቸዋል።
9
ከኀጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።
10
አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።
11
ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።
12
ደስታንና ማዳንህን ስጠኝ፥ በጽኑ መንፈስም አጽናኝ።
13
መንገድህን ለኃጥኣን አስተምራቸው ዘንድ፥ ዝንጉዎችም ወደ አንተ ይመለሱ ዘንድ።
14
የመድኀኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ደስ ይለዋል።
15
አቤቱ፥ ከንፈሮችን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።
16
መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አትወድድም።
17
የእግዚአብሔር መሥዋዕት የዋህ መንፈስ ነው፥ የተዋረደውንና የዋሁን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።
18
አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምም ቅጽሮች ይታነጹ።
19
የጽድቁን መሥዋዕት፥ መባውንም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያንጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።
← Chapter 49
Chapter 51 →