bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 39
Psalms 39
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔርን በትዕግሥት ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ተመልሶ ሰማኝ፥ የልመናዬንም ቃል ሰማኝ።
2
ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግ ጭቃም አወጣኝ፥ እግሮቼንም በዓለት ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።
3
አዲስ ምስጋናን በአፌ ጨመረ፥ ይህም የአምላካችን ምስጋናው ነው፤ ብዙዎች አይተው ይፍሩ፥ በእግዚአብሔርም ይታመኑ።
4
መታመኛው የእግዚአብሔር ስም የሆነ፥ ወደ ከንቱ ነገር፥ ወደ ቍጣና ወደ ሐሰትም፥ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።
5
አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።
6
መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድሁም፤ ሥጋህን አንጻልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም።
7
በዚያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፤
8
አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”
9
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ፤ እነሆ፥ ከንፈሮችን አልከለክልም፤ አቤቱ፥ አንተ ጽድቄን ታውቃለህ።
10
ቅንነትህን በልቤ ውስጥ አልሰወርሁም፥ ማዳንህንም ተናገርሁ፤ ይቅርታህንና ምሕረትህን ከታላቅ ጉባኤ አልሰወርሁም።
11
አቤቱ አንተ ይቅርታህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ያግኙኝ።
12
ቍጥር የሌላት ክፋት አግኝታኛለችና፤ ኀጢአቶቼ ተገናኙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
13
አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ተመልከት።
14
ነፍሴን ለማጥፋት የሚወድዱ ይፈሩ፥ በአንድነትም ይጐስቍሉ፤ በእኔ ላይ ክፋትን ለማድረግ የሚወድዱ ወደ ኋላቸው ይመለሱ፥ ይፈሩም።
15
እሰይ፥ እሰይ የሚሉኝ እፍረታቸውን ወዲያውኑ ይከፈሉ።
16
አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው፥ ሐሤትንም ያድርጉ፤ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወዱ ዘወትር፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ።
17
እኔ ድሃና ምስኪን ነኝ፥ እግዚአብሔር ግን ያስብልኛል፤ አንተ ረዳቴና መድኀኒቴ ነህ፤ አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ።
← Chapter 38
Chapter 40 →