bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 38
Psalms 38
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
“በአንደበቴ እንዳልስት አፌን እጠብቃለሁ፤ ኃጥኣን በፊቴ በተቃወሙኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ” አልሁ፤
2
ዝም አልሁ ራሴንም አዋረድሁ፥ ለበጎ ነገርም ዝም አልሁ፥ ቍስሌም ታደሰብኝ።
3
ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ፤ ከመናገሬም የተነሣ እሳት ነደደ፥ በአንደበቴም ተናገርሁ፦
4
“አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ” አልሁ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል ናቸው? ዐውቅ ዘንድስ ለምን ወደ ኋላ እላለሁ?
5
እነሆ፥ ዘመኖቼን አስረጀሃቸው፤ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉ ከንቱ ነው።
6
ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመላለሳል፥ ነገር ግን በከንቱ ይታወካሉ። ያከማቻሉ የሚሰበስቡለትንም አያውቁም።
7
አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።
8
ከኀጢአቴ ሁሉ አዳንኸኝ፥ ለሰነፎችም ስድብ አደረግኸኝ።
9
ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም። አንተ ፈጥረኸኛልና፤
10
መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥ ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና።
11
በተግሣጽህ ስለ ኀጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥ ሰውነቱንም እንደ ሸረሪት አቀለጥኻት፤ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በከንቱ ይታወካሉ።
12
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም አድምጥ፥ ቸልም አትበለኝ፤ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶችም ሁሉ እንግዳ ነኝና።
13
ወደማልመለስበት ሳልሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ።
← Chapter 37
Chapter 39 →