bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 20
Psalms 20
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ በኀይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤ በማዳንህም እጅግ ሐሤትን ያደርጋል።
2
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው፥ የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም።
3
በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፤ ከክቡር ዕንቍ የሆነ ዘውድንም በራሱ ላይ አኖርህ።
4
ሕይወትን ለመነህ፥ ሰጠኸውም፥ ለረዥም ዘመን ለዘለዓለሙ።
5
በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብርንና ምስጋናን ጨመርህለት።
6
የዘለዓለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥ በፊትህም ደስታ ደስ ታሰኘዋለህ።
7
ንጉሥ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፥ በልዑልም ምሕረት አይናወጥም።
8
እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታግኛቸው፥ ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታግኛቸው።
9
ፊትህ በተቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤ አቤቱ፥ በቍጣህ አውካቸው፥ እሳትም ትብላቸው።
10
ፍሬያቸውን ከምድር፥ ዘራቸውንም ከሰው ልጆች አጥፋ።
11
ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ መወሰን የማይቻላቸውንም ምክር ዐሰቡ።
12
ወደ ኋላቸው ትመልሳቸዋለህ፤ ፊታቸውን ለመዓትህ ጊዜ ታዘጋጃለህ።
13
አቤቱ፥ በኀይልህ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጽናትህንም እናመሰግናለን፤ እንዘምርማለን።
← Chapter 19
Chapter 21 →