bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 16
Psalms 16
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ጽድቄን ስማኝ፥ ልመናዬንም አድምጠኝ፤ በተንኰለኛም ከንፈር ያልሆነውን ጸሎቴን አድምጠኝ፤
2
ፍርዴ ከፊትህ ይወጣል፥ ዐይኖቼም ጽድቅህን አዩ።
3
በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው፥ ፈተንኸኝ፥ ዐመፅም አልተገኘብኝም።
4
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር፥ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።
5
ሰኰናዬ እንዳይናወጥ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
6
እግዚአብሔር ሰምቶኛልና እኔ ጮኽሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ቃሌንም ስማ።
7
ቀኝህን ከሚቃወሟት፥ የሚያምኑብህን የሚያድናቸውን ቸርነትህን ግለጠው።
8
እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፤
9
ከሚያጐሳቍሉኝ ኃጥኣን ፊት፥ ጠላቶቼ ግን ነፍሴን ተመለከትዋት፤
10
አንጀታቸውን ቋጠሩ፥ አፋቸውም ትዕቢትን ተናገረ።
11
አሁንም አባረሩኝ፤ ከበቡኝም፤ ዐይናቸውንም ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደረጉ።
12
እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚሸምቅ አንበሳ፥ ተሰውሮም እንደሚኖር እንደ አንበሳ ግልገል ተቀበሉኝ።
13
አቤቱ፥ ተነሥ፥ ደርሰህ አሰናክላቸው፤ ነፍሴንም ከጦር አድናት።
14
ሰይፍህ በእጅህ ጠላቶች ላይ ናት። አቤቱ፥ በምድር ካነሱ ሰዎች፥ በሕይወታቸው ከፋፍላቸው፥ ከሰወርኸው ሆዳቸው ጠገበች፤ ልጆቻቸው ጠገቡ። የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ተዉ።
15
እኔ ግን በጽድቅህ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን በማየትም እጠግባለሁ።
← Chapter 15
Chapter 17 →