bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 15
Psalms 15
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።
2
እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ ጌታዬ ነህ፤ በጎነቴን አትሻትምና።
3
ፈቃድህ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳን ላይ ተገለጠ።
4
ደዌያቸው በዛ፤ ከዚያም በኋላ ተፋጠኑ፤ በደም ማኅበራቸው አልተባበርም። ስማቸውንም በአፌ አልጠራም።
5
እግዚአብሔር የርስቴ ዕድል ፋንታና ጽዋዬ ነው፥ ርስቴን የምትመልስ አንተ ነህ።
6
ይይዙኝ ዘንድ ገመድ ጣሉብኝ፥ ርስቴ ግን ተያዘልኝ።”
7
እንዳስተውል ያደረገኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፤ ደግሞም በሌሊት ኵላሊቶች ይገሥጹኛል።
8
ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ እንዳልታወክ በቀኜ ነውና።
9
ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፥ ምላሴም ሐሤት አደረገ፤ ሥጋዬ ደግሞ በተስፋው ያድራል፤
10
ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ጻድቅህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።
11
የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘለዓለም ፍስሓ አለ።
← Chapter 14
Chapter 16 →