bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 123
Psalms 123
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦
2
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
3
የመዓት ቍጣቸውን በላያችን ባነሡ ጊዜ፥ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፥
4
በውኃ ባሰጠሙን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፤
5
ነፍሳችንም ከጐርፍ አመለጠች፤ ነፍሳችን ከክርክር ውኃ አመለጠች፤
6
ወደ ከባቢ ወጥመዳቸው ያላገባን እግዚአብሔር ይመስገን።
7
ሰውነታችን ግን እንደ ወፍ ከአዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመድ ተሰበረች፥ እኛ ግን ዳን።
8
ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር ስም ነው።
← Chapter 122
Chapter 124 →