bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 115
Psalms 115
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በተናገርሁት አመንሁ፤ እኔም እጅግ ታመምሁ።
2
እኔም ከራሴ ጀምሮ፥ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።
3
ስላደረገልኝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምንን እከፍለዋለሁ?
4
የሕይወትን ጽዋ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
5
በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ።
6
የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።
7
አቤቱ፥ እኔ ባሪያህ ነኝ፥ ባሪያህ ነኝ፥ የሴት ባሪያህም ልጅ ነኝ፤ ሰንሰለቴን ሰበርህ።
8
ለአንተ የምስጋና መሥዋዕትን እሠዋለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
9
በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ፥
10
በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በመካከልሽም። ሃሌ ሉያ።
← Chapter 114
Chapter 116 →