bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 114
Psalms 114
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት።
2
ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።
3
የሞት ጣር ያዘኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፤ ጭንቀትና መከራ አገኘኝ።
4
የእግዚአብሔርንም ስም ጠራሁ፦ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።
5
እግዚአብሔር መሓሪና ጻድቅ ነው። አምላካችን ይቅር ባይ ነው።
6
እግዚአብሔር ሕፃናትን ይጠብቃል፤ ተቸገርሁ እርሱም አዳነኝ።
7
ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥ እግዚአብሔር ረዳትሽ ነውና፤
8
ነፍሴን ከሞት፥ ዓይኔንም ከእንባ፥ እግሬንም ከድጥ አድኖአልና።
9
በሕያዋን ሀገር እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ።
← Chapter 113
Chapter 115 →