bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Hosea 13
Hosea 13
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ኤፍሬም እንደ ተናገረ በእስራኤል ሥርዐቱን ወሰደ፤ ለበዓልም አደረገው፤ ሞተም።
2
ዳግመኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚሠራው አምሳል ከወርቃቸውና ከብራቸው ጣዖትን ሠሩ፤ እንዲህም አሉ “ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አልቋል።”
3
ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋት እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፋስም ከዐውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከምድጃም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።
4
ሰማይን ያጸናሁ፥ ምድርንም የፈጠርሁ፥ እጆችም የሰማይ ሠራዊትን ያቆሙ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እንዳትከተላቸውም እነርሱን አላሳየሁህም። ከግብፅ ምድርም ያወጣሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አትወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚያድንህ የለምና።
5
በምድረ በዳና በዞርህበት ምድር ሁሉ ጠበቅሁህ።
6
ከተሰማራችሁ በኋላ ጠገባችሁ፤ በጠገባችሁም ጊዜ ልባችሁ ታበየ፤ ስለዚህም ረሳችሁኝ።
7
ስለዚህም ለይሁዳ ቤት እንደ አንበሳ፥ ለኤፍሬምም እንደ ነብር ሆንሁባቸው።
8
በአሦራውያንም መንገድ አጠገብ እንደ ተራበ ድብ እገጥማቸዋለሁ፤ የልባቸውንም ሥር እቈርጣለሁ፤ በዚያም የዱር አንበሶች ይበሏቸዋል፤ የምድረ በዳም አራዊት ይነጣጠቋቸዋል።
9
እስራኤል ሆይ! በመከራህ ጊዜ ማን ይረዳሃል?
10
ንጉሥህ ወዴት አለ? በየከተማህ ሁሉ እስኪ ያድንህ! ንጉሥና አለቃ ስጠኝ የምትለኝ እስኪ እነርሱ ይበቀሉልህ?
11
በቍጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤ በመዓቴም ሻርሁት።
12
የዐመፅህን ወንጀል ታገሥሁት፤ የኤፍሬም ኀጢአቱም ተከማችትዋል ።
13
ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይዘዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋቂም አይደለም፤ በልጆችም ተግሣጽ አይጸናም።
14
ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፤ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! ድል መንሣትህ ወዴት አለ? ደስታህ ከዐይኖችህ ተሰወረች።
15
ከወንድሞቹ መካከል ይለያል፤ እግዚአብሔርም ከምድረ በዳ የሚያቃጥል ነፋስን ያመጣል፤ ሥሩን ያደርቃል፤ ምንጩንም ያነጥፋል፤ ምድርን ያደርቃል፤ የተወደዱ ዕቃዎችንም ሁሉ ያጠፋል።
← Chapter 12
Chapter 14 →