bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Hosea 12
Hosea 12
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤል ቤትና ይሁዳም በተንኰል ከበቡኝ፤ አሁንም እግዚአብሔር ዐወቃቸው፤ ለእግዚአብሔርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ።
2
ኤፍሬም ግን ክብርንና ከንቱ ነገርን የሚያሳድድ ክፉ ጋኔን ነው። ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፤ ከአሦርም ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ ምሕረትም ያደርጉለት ዘንድ ወደ ግብፅ ዘይትን ይልካል።
3
እግዚአብሔርም ደግሞ ከይሁዳ ጋር ይዋቀሳል፤ ያዕቆብንም እንደ መንገዱ ይበቀለዋል፤ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።
4
በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፤ በደካማነቱም ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ።
5
ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነኝ። በቤትአዎንም አገኘኝ፤ በዚያም ከእኔ ጋር ተነጋገረ።
6
ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር መታሰቢያው ነው።
7
ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ምሕረትንና ፍርድን ጠብቅ፤ ዘወትርም ወደ አምላክህ ቅረብ።
8
በከነዓን እጅ የዐመፅ ሚዛን አለ፤ ቅሚያንም ይወድዳል።
9
ኤፍሬምም፥ “ባለጸጋ ሆኜአለሁ፤ ሀብትንም አግኝቻለሁ፤ በድካሜም ሁሉ ኀጢአት የሚሆን በደል አይገኝብኝም” አለ።
10
እኔም ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንደ ዓመት በዓል ቀንም እንደ ገና በድንኳን አስቀምጥሃለሁ።
11
ለነቢያትም ተናግሬአለሁ፤ ራእይንም አብዝቻለሁ፤ በነቢያትም እጅ ተመስያለሁ።
12
በገለዓድ ባይሆንም እንኳ በጌልጌላ መሥዋዕታቸውን የሚሠዉ አለቆች ስተዋል፤ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልም ላይ እንደ አለ የድንጋይ ክምር ነው።
13
ያዕቆብ ወደ ሶርያ ሀገር ሸሸ፤ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፤ ስለ ሚስትም ጠበቀ።
14
እግዚአብሔርም በነቢይ እስራኤልን ከግብፅ ምድር አወጣው፤ በነቢይም ጠበቀው።
15
ኤፍሬም ተመረረ፤ ተቈጣም፤ ደሙም በላዩ ላይ ይፈስሳል፤ እግዚአብሔርም ስድቡን በራሱ ላይ ይመልሳል።
← Chapter 11
Chapter 13 →