1 Kings 16

Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

28ዘን​በ​ሪም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት፤ ልጁም አክ​አብ በፋ​ን​ታው ነገሠ። ‘ሀ’ ዘን​በ​ሪም ዐሥራ አንድ ዓመት ሲሆ​ነው የአሳ ልጅ ኢዮ​ሳ​ፍጥ ነገሠ። በነ​ገ​ሠም ጊዜ ሠላሳ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ አም​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ጋዙባ የም​ት​ባል የሴ​ላህ ልጅ ነበ​ረች። ‘ለ’ በአ​ባ​ቱም በአሳ መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ጽድ​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ ከእ​ር​ስዋ ፈቀቅ አላ​ለም። በተ​ራ​ሮች የነ​በ​ሩ​ት​ንም አማ​ል​ክት አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም በተ​ራ​ሮቹ ይሠ​ዉ​ላ​ቸ​ውና ያጥ​ኑ​ላ​ቸው ነበረ። ‘ሐ’ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ጋር የሠ​ራው፥ የተ​ዋ​ጋ​ውና ያደ​ረ​ገው ኀይል ሁሉ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው። ‘መ’ በአ​ባ​ቱም በአሳ ዘመን የነ​በ​ረ​ውን ርኵ​ሰት ሁሉ ከም​ድር አስ​ወ​ገደ። በኤ​ዶ​ምም ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም። ‘ሠ’ ንጉሥ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ወር​ቅና ብርን ሊያ​መ​ጡ​ለት ወደ አፌር ይልክ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከብ አሠራ፤ በጋ​ስ​ዮንጋቤር የነ​በ​ረ​ችው መር​ከብ ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም። ‘ረ’ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥን፥ “አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮቼን በመ​ር​ከብ እን​ላክ” አለው። ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እንቢ አለ። ‘ሰ’ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ። በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።
← Chapter 15Chapter 17 →