bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Bible (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
/
Job 17
Job 17
Amharic Bible (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
1
መንፈሴ ደከመ፥ ዘመኔ አለቀ፥ መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።
2
አላጋጮች በእኔ ዘንድ አሉ፥ ዓይኔም በማስቈጣታቸው አደረች።
3
አሁንም አንተ መያዣ ሆነህ ተዋሰኝ፤ ከእኔ ጋር አጋና የሚመታ ማን ነው?
4
ልባቸውም እንዳያስተውል ከልክለኸዋል፤ ስለዚህ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም።
5
ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ የልጆቹ ዓይን ይጨልማል።
6
ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፤ በፊቱ ላይ ጺቅ እንደሚሉበት ሰው ሆንሁ።
7
ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ ብልቶቼም ሁሉ እንደ ጥላ ሆኑ።
8
ቅኖች ሰዎች በዚህ ነገር ይደነቃሉ፥ ንጹሕም በዝንጉው ላይ ይበሳጫል።
9
ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።
10
ነገር ግን እናንተ ሁሉ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ፤ በእናንተም ዘንድ ብልሃተኛ አላገኝም።
11
ዕድሜዬ አለፈች፤ አሳቤና የልቤ መሣርያ ተቈረጠ።
12
ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ ብርሃኑም ወደ ጨለማ የቀረበ ይመስላቸዋል።
13
ተስፋ ባደርግ ሲኦል ቤቴ ናት፤ ምንጣፌንም በጨለማ ዘርግቻለሁ።
14
መበስበስን። አንተ አባቴ ነህ፤ ትልንም። አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ።
15
እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው?
16
አብረን በመሬት ውስጥ ስናርፍ፥ ወደ ሲኦል ይወርዳል።
← Chapter 16
Chapter 18 →