bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Zechariah 13
Zechariah 13
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
2
በዚያን ጊዜ የጣዖቶችን ስሞች ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ፤ ዳግመኛም የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ የጣዖት ነቢያትንና ርኩሳን መናፍስትን አስወግዳለሁ።
3
ማንም ነቢይ ነኝ ብሎ ቢነሣ የወለዱት አባቱና እናቱ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ስለ ተናገርክ መሞት አለብህ ይሉታል፤ ትንቢትም ሲናገር ወላጆቹ ወግተው ይገድሉታል።
4
በዚያን ጊዜ ማንኛውም ነቢይ ነኝ ባይ በሚያየው ትንቢታዊ ራእይ ያፍርበታል፤ ሰዎችንም ለማታለል ጠጒር ያለበትን ልብስ ለብሶ አይታይም።
5
እኔ ገበሬ ነኝ እንጂ ነቢይ አይደለሁም፤ ከወጣትነቴ ጀምሮ የእርሻ መሬት ባለቤት ነኝ ይላል።
6
አንድ ሰው ‘ታዲያ ይህ በሰውነትህ ላይ ያሉት ቊስሎች ምንድን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቀው ‘በወዳጄ ቤት የቈሰልኩት ነው’ ብሎ ይመልስለታል።”
7
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።
8
በአገሪቱ ላይ ካሉት ሕዝቦች ከሦስቱ ሁለቱ እጅ ተመተው ይሞታሉ፤ ሆኖም ከሦስቱ አንዱ እጅ ይቀራል።
9
እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”
← Chapter 12
Chapter 14 →